የሶስተኛ ወገን የኃላፊነት ሕጋዊ ግዴታ መድን Public Liability Policy ዋስትና ለማግኘት መሟላት ያለባቸው መረጃዎች፣ |
· በድርጅቱ የተዘጋጀውን የውል መጠየቂያ ቅጽ በጥያቄው መሠረት በጥንቃቄ መሙላት፣· ሌሎች መረጃዎች ወይም ሠነዶች እንደ አስፈላጊነቱ ሊጠየቁ ይችላሉ፡፡ በሶስተኛ ወገን የኃላፊነት ሕጋዊ ግዴታ መድን (Public Liability Policy) ለሚደርስ አደጋዎች መቅረብ ያለባቸው ዋና ዋና ማስረጃዎች 1.1 በሰው ላይ ለሚደርስ የሞት አደጋን በሚመለከት፣ 1.1.1 የፖሊስ ሪፖርት ማቅረብ፣ 1.1.2 አደጋው እንደደረሰ ስለአደጋው ለሚመለከተው ቅርንጫፍ ማሳወቅ፣ 1.1.3 የአሟሟቱን ሁኔታ የሚገልጽ የሬሣ ምርመራ የሐኪም ማስረጃ ማቅረብ፣ 1.1.4 የሕጋዊ ወራሾች የፍርድ ቤት ውሳኔ ማቅረብ፣ 1.2 በሰው ላይ ለሚደርስ የአካል ጉድለት 1.2.1 ለቋሚ የአካል ጉድለት የህክምና ቦርድ ማስረጃ ማቅረብ፣ 1.2.2 ለሕመም ፈቃድ የሀኪም ማስረጃ ማቅረብ፣ 1.2.3 መድኃኒት እንዲገዛ ሐኪም ያዘዘበት ማስረጃ ማቅረብ፣ 1.2.4 መድኃኒት የተገዛበትና የህክምና ወጪ ሕጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ፣ 1.2.5 የሕክምና ማስረጃ ሠርተፊኬት ማቅረብ፣ 1.3 በንብረት ላይ ለሚደርስ ጉዳት /የደረሰበት ንብረት ዝርዝርና ግምታዊ ዋጋ/፣ 1.3.1 ከፖሊስ/ሕዝባዊ ድርጅት ሪፖርት ማቅረብ፣ 1.3.2 ስለጉዳት መጠኑ የባለሙያ ግምት ማቅረብ፣ 1.4 በጠፋው ንብረት ለድርጅቱ የመዳረግ መብት (Subrogation Right) መስጠት፣ 1.5 ከጉዳት የተረፈውን ንብረት በጥንቃቄ ማስቀመጥና እንዲጠበቅ ማድረግ፣ · ሌሎች መረጃዎች ወይም ሰነዶች እንደ አስፈላጊነቱ ሊጠየቁ ይችላል፡፡ |