የኢትዮጵያ መድን ድርጅት የእግር ኳስ ቡድን ወደ ፕሪምየር ሊግ ማደጉን አስመልክቶ የምስጋና እና የዕውቅና መርሐ-ግብር አደረገ።
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት እግርኳ ስቡድን በ 2014 ዓ.ም ሲወዳደርበት የቆየውን ከፍተኛ ሊግ ውድድር ከምድቡ አሸናፊ በመሆን የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን መቀላቀሉን አስመልክቶ ለክለቡ ተጫዋቾች እና ባለድርሻ አካላት ግንቦት 30 ቀን 2014 ዓ.ም በሂልተንሆ ቴል የምስጋና እና የዕውቅና መርሐ-ግብር አከናወነ፡፡
በዝግጅቱ ላይ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዝናቡ ይርጋ፣ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ነጻነት ለሜሳና ሌሎች የድርጅቱ ም/ዋናሥራ አስፈጻሚዎች፣ የስፖርት ማህበሩ ኮሚቴ አባላት እና ከፍተኛ የሥራ አመራር አባላት በተገኙበት የዕውቅና እና የሽልማት መርሐ-ግብርተ ካሂዷል፡፡
አቶ ነጻነት ለሜሳ በእውቅና አሰጣጥ ዝግግቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸውም የስፖርት ማህበሩ ከተመሰረተበት ከ1975 ዓ.ም ጀምሮ በእግርኳስ፣ በውሃዋ ና፣ በአትሌቲክስና በመሳሰሉት የስፖርት ዘርፎች ተወዳዳሪዎችን በመያዝ የኢትዮጵያን ስፖርት ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ግንባር ቀደም መሆኑን ንበመጥቀስ ላለፉት አስርት ዓመታት ትኩረቱን በእግር ኳስ ላይ በማድረግ የስፖርት ማዕከል በማደራጀት፣ የተለያዩ መወዳደሪያ ሜዳዎችና የስፖርተኞች ማደሪያ፣ መመገቢያና መዝናኛ በማዘጋጀት ለክለ ቡውጤታማነት ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን ጠቅሰዋል፡፡
አቶ ነጻነት ለሜሳ በዕውቅና መርሐ-ግብሩ ላይ ንግግር ሲያደርጉ
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት የእግር ኳስ ቡድን በአገራችን ውስጥ ከሚገኙ ጠንካራና ውጤታማ ቡድኖች መካከል አንዱ እንዲሆን ድርጅቱ ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን በመግለጽ ቡድኑ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ በ1984፣በ1987፣በ1989 እና በ1994 ዓ.ምየ ክልል 14 እና የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ የእግር ኳስ ውድድሮችን አራት ጊዜ ድል በመቀዳጀት በአገር ውስጥ ውድድሮች ጠንካራ ተፎካካሪነቱን ከማስመስከሩ ባሻገር በአህጉር አቀፍ ደረጃበ ተወዳደረባቸው መድረኮች ያስመዘገበው ያልተደፈረ ውጤት በእጅጉ የሚያኮራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ዋና ሥራ አስፈጻሚው አክለውም ቡድኑ አሁን ያገኘውን ድል አጠናክሮ በመያዝ በቀጣዩ የውድድር ዘመን በፕሪምየር ሊጉ ውስጥ በሚካሄደው ውድድር ብቁ ተወዳዳሪ፣ ጠንካራ ተፎካካሪና የዋንጫ ባለቤት ለመሆን ጭምር በቁርጠኝነት መሥራት ስለሚኖርበት በዚህ ሂደት ውስጥ በተለይ የተጫዋቾችና፣ የአሰልጣኞች፣ ጠንካራ ሥራ እንዲሁም የደጋፊውና የመላው ሠራተኛ ከፍተኛ ተሳትፎና የቅርብ ዕገዛ ለውጤቱ ማማር ወሳኝ ሚና ያለው መሆኑን በመግለጽ ንግግራቸውን ቋጭተዋል፡፡
በዕውቅና እና በምስጋና መርሐ-ግብሩ ላይ ድርጅቱ ለጽ/ቤት ሠራተኞች፣ የስልጠና ቡድን አባላት፣ የቡድኑ አግር ኳስ ተጫዎቾች እንዲሁም የስፖርት ማህበሩ ሥራአ ስፈጻሚ ኮሚቴ ከብር ሰላሳ ሺህ እስከ ሦስት መቶ ሺህ የሚደርስ የገንዘብ ሽልማት የተበረከተ ሲሆን ለአምስት የስፖርት ማህበሩ የቦርድ አባላት ለእያንዳንዳቸው በአይነት ሽልማት የተሰጠ ሲሆን በዚህም ድርጅቱ በአጠቃላይ ብር ስድስት ሚሊዮን የሚጠጋ ወጭ እንዳወጣ ተገልጿል፡፡
የሽልማት ሂደቱ በከፊል