የህይወት መድን ዋስትና
የኢትጵያ መድን ድርጅት በህይወት መድን ዘርፍ አገልግሎት ላይ የዋላቸው የመድን አይነቶች ከ15 ዓይነት በላይ ናቸው፡፡ የህይወት መድን ዋስትናዎች የተለያዩ ጠቀሜታዎች የሚያስገኙ ሲሆን በግል ወይም በቡድን ልገዙ የሚችሉ የዋስትና አይነቶች አሉ፡፡ ዋስትናዎቹ የሚያስገኙት ጠቀሜታ መሰረት የሚያደርገው ደንበኞች የሚከፍሊትን የአለቦን መጠን ሲሆን ለተለያዩ ዕዳዎች ማወራረጃ (Protection) የሚያገለግሉ ይገኙበታል፡፡ ድርጅቱ ከሚሸጣቸው የሕይወት መድን ዋስትና ውስጥ፡-
• ኢንዶውመንት (መደበኛ፣ ትርፍ አካፋይ አንቲሲፔትድ፣ ትርፍ አካፋይ የልጆች የትምህርት፣ አሊዩቲ ወዘተ)
• ተርም የመድን ዋስትና፣ (የግል፣ የቡድንና የትላልቅ ቡድኖች እንዲሁም የግል፣የቡድንና የጣምራ የባንክ የቀሪ እዳ ማወራረጃ፡፡
• የእድሜ ልክ የመድን ዋስትና፣
• የህክምና የመድን ዋስትና (የግል፣ የቡድን፣ የከፍተኛ ኃላፊዎች፣ የተጓጓዦች ህክምና) ወዘተ ይገኙበታል፡፡
ድርጅቱ በሕይወት መድንም የተለያዩ የህብረተሰቡን የኢኮኖሚና ማህበራዊ ሁኔታዎች ያገናዘቡ ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የሚያገለግሉ ዋስትናዎችን ቀርፆ ያቀርባል፡፡ ከዚህም አንፃር በምሳሌነት የሚጠቀሰው የቀብር ማስፈፀሚያ (pre-need funeral expense) ዋስትና ነው፡፡
ህይወት ነክ ያልሆነ የመድን ዋስትና
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ከ30 በላይ ሕይወት ነክ ያልሆኑ የመድን ዋስትናዎችን ይሰጣል፡፡ ሕይወት ነክ ያልሆኑ ዋስትናዎች የሚያገለግሉት ለንብረትና ለህጋዊ ኃላፊነት ነው፡፡ ድርጅቱ ዋስትናዎቹን በየጊዜው በመፈተሸ የማሻሻል ሥራ (revise) ያከናውናል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የወቅቱ የአገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት የሚጠይቀውንና በደንበኞች ፍላጎት ላይ የተመሰረተ አዳዲስ የዋስትና ዓይነቶችን በመቅረፅ ገበያ ላይ ያውላል፡፡
ለአብነት ያህል በአሁኑ ጊዜ፣የአበባ፣ የጋራ መኖሪያ ቤት፣ የቡናና ሻይ፣በዝናብ እጥረት ለሚደርስ የምርት መቀነስ፣ ለግብርና ውጤቶች የመጋዘን ባለቤቶች የክምችት ኃላፊነት የሚያገለግሉ ዋስትናዎች ቀርፆ አቅርቧል፡፡ ድርጅቱ በዋናነት ከሚሰጣቸው የንብረትና የኃላፊነት ዋስትናዎች ውስጥ የማንኛውም አደጋ፣የአዬሸን (ለጭነቱና ለአይሮፕላኑ)፣ የባንኮች ሁሉን አቀፍ ዋስትና፣ ቤት ሰብሮ ለሚፈፀም ዝርፊያ፣ የቦንድ፣ የጋራ መኖሪያ ቤት፣ የትርፍ እጦት፣ የአዝርዕት፣ የኢንጂነሪንግ፣ የእምነት ማጉደል፣የእሳትና የመብረቅ፣ በትራንዚት ለሚተላለፉ ዕቃዎች፣ የአጓጓዦች ኃላፊነትጓ የእንስሳት፣ የማሪን፣ (ለጭነቱና ለመርከቡ)፣የገንዘብ፣ የተሸከርካሪ፣ የግል (የቡድን አደጋ፣ የመስታወት፣ የምርት ኃላፊነት፣ የሙያ፣ የሦስተኛ ወገን (ሕጋዊ) ኃላፊነት፣ የሠራተኛ ጉዳት ካሣ እና ሌሎች የመድን ዋስትናዎች ይገኙበታል፡፡