Motor

በተሽከርካሪ መድን ደንበኛው ውል ሲገቡ መጤን ያለባቸው ዋና ነጥቦች

1. ድርጅታችን የሚሰጠው የሽከርካሪ መድን ዋስትና አይነቶችሀ. አጠቃላይ መድን ዋስትና፣

ለ. በሶስተኛ ወገን ላይ ለሚደርስ አደጋ ዋስትናና ተሽከርካሪው ላይ ለሚደርስ የእሳትና የስርቆት አደጋ ዋስትና፣

ሐ. በሶስተኛ ወገን ላይ ለሚደርስ አደጋ ዋስትና ናቸው፡፡

መ. የተሳፋሪና፣ ¼PAB & PLL¼ የሽፍታ /BSG/ ሽፋን በተጨማሪ ማግኘት ይችላሉ፡፡

2. ስለሶስቱም የዋስትና አይነቶች አጭር መግለጫ ካገኙ በኋላ የተሽከርካሪ ባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር /ሊብሬ/ መያዝዎን ወይም ወኪል ከሆኑ የውክልና ሰነድ መያዝዎን ያረጋግጡ፡፡

3. በውል እድሳት ወቅት ቀጣይ ዋስትና ለማግኘት ይቻል ዘንድ ማስታወሻ በአድራሻዎ አማካኝነት አስቀድሞ ይላክልዎታል፡፡ ወዲያውኑ ውሉ እንዲታደስ ፈቃደኛ መሆንዎን ፈርመው መላክ ይጠበቅብዎታል፡፡

4. ውል በሚገቡበት ጊዜ ተሽከርካሪዎ የቅድመ አደጋ ምርመራ መደረግ ስላለበት ተሽከርካሪውን ማቅረብ ይኖርቦታል፡፡ /የድርጅት ተሽከርካሪዎችን አይመለከትም/

5. የተሽከርካሪውን ዝርዝር መግለጫ የመድን መግበያ መጠየቂያ ቅጹ (proposal form) በሚጠይቀው መሠረት ትክክለኛውን መረጃ ያምጡ፣ አድራሻ ለውጥ እንዳደረጉ ወዲያውኑ ለድርጅቱ ያሳውቁ፡፡

6. በተሽከርካሪዎ ላይ አደጋ ደርሶ በውሉ መሠረት የካሣ ክፍያ ሲጠየቁ በውሉ ለይ የተገለጸው የአደጋ መነሻ (Excess) ክፍያ በእርስዎ እንደሚሸፈን አይዘንጉ፡፡

7. በውሉ ዘመን ውስጥ አደጋ ካላደረሱ በዕድሳት ወቅት የአረቦን ቅናሽ እንደ¸Ãsg”Lã ይገንዘቡ፡፡ በተጨማሪም በፈቃደኝነት የአደጋ መነሻ (voluntary excess) ከተቀበሉ የአረቦን ቅናሽ እንደ¸ÃSg”Lã ይገንዘቡ፡፡

8. ተሽከርካሪዎ ለጥገና ሲቆም (laid up) ውሉን ማቋረጥና ተጠግኖ ሲወጣ ውሉን መቀጠል ይኖርብዎታል፡፡ የቆይታ ጊዜውን በሚመለከት የግል ተሽከርካሪ ቢያንስ ከውል ዘመን ውስጥ ለአራት ተከታታይ ሳምንታት፣ የጭነት ተሽከርካሪ ለአሥራ ሁለት ተከታታይ ሳምንታት መቆየት ይኖርበታል፡፡

9. መድን የሚገባለት ተሽከርካሪዎ ከቀረጥ ነፃ ከሆነ ዋጋውን ለመተመን እንዲያስችል ከጉምሩክ የቀረጥ መጠኑን ማቀረብ ይጠበቅቦታል፡፡

10. ተሽከርካሪዎን ለመንዳት የሚያስችል ሕጋዊ መንጃ ፈቃድ ሳይዙ ማሽከርከር እና ከተፈቀደው ጭነት በላይ ጭኖ ማሽከርከር እንዲሁም ዋስትና ያልተገባለት ተሳቢ ሲጎተት አደጋ ቢደርስ ሽፋን እንደሌለውና መሰናክል እንደሚሆኑ አይዘንጉ፡፡

11. የንግድ ተሽከርካሪን በሚመለከት ለአሽከርካሪዎ ተጨማሪ የሠራተኛ ጉዳት ዋስትና መግባት እንዳለብዎ አይዘንጉ፡፡

12. bComesa አባል አገራት ተሽከርካሪዎ በሶሶተኛ ወገን ላይ ለሚያደርሰው ጉዳት የቢጫ ካርድ በመግዛት ሽፋን የሚያገኙ መሆኑን ይገንዘቡ፣ /ወደ ጅቡቲ እና ሱዳን ክልል በተሽከርካሪው ለሚደርስ ጉዳትም ይጨምራል/ ለተሽከርካሪው አጠቃላይ ሽፋን በመግዛት የሽፋኑን መጠን ከፍ ማድረግ ይቻላል፡፡

13. ተጨማሪ ማስረጃ ወይም ሰነድ እንደ አስፈላጊነቱ ሊጠየቁ ይችላሉ፡፡

በተሽከርካሪ ላይ አደጋ ሲደርስ ደንበኛው ማሟላት ያለባቸው ዋና ነጥቦች

ካሣ

1. በንብረትዎም ሆነ በሶስተኛው ወገን አደጋ እንደደረሰ ወዲያውኑ በአቅራቢያዎ ለሚገኘው የመድን ድርጅት ቅርንጫፍ ያመልክቱ፡፡

2. የአደጋው ሁኔታ በአፋጣኝ በትራፊክ ፖሊስ፣ በድርጅቱ ኢንስፔክተር እንዲታይ ያድርጉ፣ ተገቢውን መረጃ በመሰብሰብ እና በመስጠት የበኩልዎን ድርሻ ይወጡ፡፡

3. ስለአደጋው አደራረስ በድርጅቱ በተዘጋጀው የአደጋ ማሳወቂያ ቅጽ ላይ የተሟላ መረጃ በመስጠት ስለተክክለኛነቱ በፊርማዎ ያረጋግጡ፡፡ ማንኛውንም የካሣ ጥያቄ በተመለከተ ከድርጅታችን እውቅና ውጪ ከሶስተኛ ወገን ጋር ድርድር ወይም ስምምነት ወይም ኃላፊነትን አይቀበሉ፡፡

4. ተሽከርካሪዎ የጭነት ከሆነ አደጋ ከደረሰበት ቦታ ወደ ሪከቨሪ መውሰድ እነዲቻል የተጫነውን ጭነት በማራገፍ በኩል አፋጣኝ እርምጃ ይውሰዱ፡፡

5. በንብረትዎ ላይ ጉዳት ወይም አደጋ እንደደረሰ ንብረትዎ ለበለጠ ጉዳት እንዳይጋለጥ ንብረትዎን ማስጠበቅ ይኖርብዎታል፡፡

6. ተሽከርካሪው በባለሙያው ተመርምሮ ከጥቅም ውጭ ወይም ሙሉ ውድመት ከደረሰበት አስፈላጊውን ክፍያ ለመፈጸም ይቻል ዘንድ የሚከተሉትን ሊያሟሉ ይገባል፡፡

ሀ/ የባለቤትነት መታወቂያ ደብተር /ሊብሬ/ እና ልዩ የተሽከርካሪ ምዝገባ /ለንግድ ተሽከርካሪ/ ማቅረብ፣

ለ/ ድርጅቱ ቅሪቱን ለመሸጥ ለመለወጥ የሚያስችለው ሕጋዊ ውክልና መስጠት፣

ሐ/ ከመንገድ ትራንስፖርት አስፈላጊው የተሽከርካሪ ግብር ለመክፈልዎና እዳና እገዳ እንደሌለበት ማረጋገጫ ማቅረብ፣

መ/ ከአገር ውስጥ ገቢ መ/ቤት በተሽከርካሪው ላይ የሚፈለግ ግብር አለመኖሩን የሚገልጽ ማረጋገጫ ማቅረብ፣

ሠ/ ወኪል ከሆኑ ህጋዊ የውክልና ማስረጃ ማቅረብ፣

7. በመጨረሻም ጥገናው ለመከናወኑ (Satisfaction Note) ፈርመው ተሽከርካሪውን መረከብ ይችላሉ፡፡

8. በተለይ ያገለገለ ተሽከርካሪ ላይ በጥገና ወቅት በተለዋጭ እቃዎች ላይ የሚጣለውን የእርጅና መዋጮ መክፈል፣

9. በ Comesa አባል አገራት ተሽከርካሪዎች በሶስተኛ ወገን ለሚደርሰው አደጋ ቢጫ ካርዱን ለክልሉ የኮሜሳ ቢሮ በማሳየት የካሣ መስተንግዶ ማግኘት ይችላሉ፣

10. ሌሎች መረጃዎች እንደ አስፈላጊነቱ ሊጠየቁ ይችላሉ፡፡