በዕምነት ማጉደል መድን Fidelity Guarantee Policy ዋስትና ለማግኘት መሟላት ያለባቸው መረጃዎች
- በድርጅቱ የተዘጋጀውን የውል መጠየቂያ ቅጽ በጥያቄው መሠረት በጥንቃቄ መሙላት፣
· አንድ ጊዜ የእምነት ማጉደል ያደረሰ ሠራተኛ¼‰t®C ዳግም በውሉ ሊሸፈን /ሊሸፈኑ አይችልም፣
· ሌሎች መረጃዎች ወይም ሠነዶች እንደ አስፈላጊነቱ ሊጠየቁ ይችላሉ፣
በዕምነት ማጉደል መድን (Fidelity Guarantee Policy) ለሚደርሱ አደጋዎች መቅረብ ያለባቸው ዋና ዋና ማስረጃዎች
1 . የዕምነት መጉደሉ እንደደረሰ ወዲያውኑ ለሚመለከተው ቅርንጫፍ ማሳወቅ
2 . ዕምነት ያጐደለው ሠራተኛ መተማመኛ ካልፈረመ የፖሊስ ሪፖርት፣
3 . የኦዲተር ሪፖርት ማቅረብ፣
4 . ዕምነት ያጐደለው ሠራተኛ መተማመኛ ካልሰጠ የፍርድ ቤት ውሳኔ፣
5 . ለዕምነት አጉዳዩ የሚከፈል ገንዘብ ካለ ምሳሌ ደመወዝ አበል ወዘተ የተያዘ መሆኑን ማረጋገጫ ጽሁፍ፣
6 . የዕምነት አጉዳዩ ትክክለኛ አድራሻ፣ ከተማ፣ ከፍተኛ፣ ቀበሌ፣ የቤት ቁጥር
7 . የዕምነት አጉዳዩ ተንቀሳቃሽ ወይም የማይንቀሳቀስ ንብረት ካለው እንዲገለጽ ማድረግ፣
8 . ለጠፋው ገንዘብ ለድርጅቱ የመዳረግ መብት (Subrogation Right) መስጠት፣
· ሌሎች መረጃዎች ወይም ሰነዶች እንደ አስፈላጊነቱ ሊጠየቁ ይችላል፡፡