Bond

የጨረታ፣ የመልካም ሥራ አፈጻጸም፣ የጥገና፣ የቅድሚያ ክፍያና የቀረጥ ቦንድ ለማግኘት መሟላት ያለባቸው መረጃዎች

· የደንበኛው ስምና አድራሻ፣

· የአሠሪው ስምና አድራሻ፣

· የቦንድ አይነት፣

· ጠቅላላ የቦንድ ዋጋ፣

· አሁን የተጠየቀው የቦንድ ዋጋ፣

· የቦንድ ውል ዘመን ከ……………….. እስከ ………………..

· የተጠየቀው ቦንድ ሥራ ከአሠሪው መ/ቤት ጋር የተደረገ የውል ስምምነት ሰነድ (Contract agreement) ፎቶ ኮፒ ይቅረብ፣

· ለተጠየቀው ቦንድ የሚውል ተመጣጣኝ መያዣ (Collateral) በቅድሚያ ማስያዝና ይህንም በሕግ ፊት እንዲጸና ¥DrG½

· የተያዘው መያዣ ባለንብረቱና በመድን መ/ቤት ስም ዋስትና መግባት ያለበት መሆኑን ዋስትናውም ደንበኛው ከአሠሪው መ/ቤት ጋር ባደረገው የውል ስምምነት መሠረት የዋስትና ሽፋኑ የጊዜ ገደብ በየዓመቱ በእድሳት ተጠብቆ እንዲቆይ ¥DrG½

· የቦንዱ ሥራ ካለቀ ኦሪጅናል ቦንዱ ተመላሽ ማድረግ፡፡ ወይም አሠሪው በተሰጠው ቦንድ ላይ የካሣ ጥያቄ የሚያቀርብ መሆኑን የጽሑፍ ማረጋገጫ ¥QrB½

· ሌሎች መረጃዎች ወይም ሰነዶች እንደ አስፈላጊነቱ ሊጠየቁ ይችላል፡፡

በጨረታ፣ በመልካም ሥራ አፈጻጸም፣ በጥገና እና በአቅርቦት መድን (Bid, performance, maintenance and supply Bonds) ለሚደርሱ አደጋዎች መቅረብ ያለባቸው ዋና ዋና ማስረጃዎች

1.1 የጨረታ መድን (Bid Bond) በሚመለከት 

1.1.1 የጨረታ ተሳታፊዎች ስም ዝርዝርና እያንዳንዱ ተጫራች የተጫረተበትን  ገንዘብ መጠን ማሳወቅ፣

1.1.2 ለጨረታ አሸናፊው በጨረታው ውል መሠረት አሸናፊነቱ ተገልጾ የተጻፈለት ደብዳቤ ኮፒ ¥QrB¼መስጠት፣

1.1.3 በጨረታ አሸናፊነቱ በጨረታው ውል መሠረት ፈቃደኛ ካልሆነ ፈቃደኛ ላልሆነበት ምከንያት የጽሑፍ ማስረጃ ማቅረብ፣

1.1.4 ለድርጅቱ የመዳረግ መብት (Subrogation Right) መስጠት፣

1.2 የመልካም ሥራ አፈጻጸምና ጥገና የአቅርቦት መድን (Performance, maintenance and supply bonds) 

1.2.1 የሥራ ተቋራጩ (Contractor) በገባው ውል መሠረት ሥራውን ባለማከናወኑ ሥራውን እንዲያከናውን የተሰጠው ማስጠንቀቂያ ጽሑፍ ኮፒ ማቅረብ፣

1.2.2 የሥራ ተቋራጩ በሥራው ውል መሠረት ገዴታውን ሊወጣ ያልቻለበት ምክንያትና ያላከናወነውን ሥራ ዝርዝር የጽሑፍ ማስረጃ ማቅረብ፣

1.2.3 ለሥራ ተቋራጩ ለሰራው ሥራ የተከፈለውና ያልተከፈለው ቀሪ ገንዘብ ምን ያህል እንደሆነ ተለይቶና እንዲሁም ለተከፈለው ገንዘብ የሰጠው ደረሰኝ ተያይዞ የጽሑፍ ማስረጃ ማቅረብ፣

1.2.4 በሥራ ውሉ መሠረት በየጊዜው የሥራ አፈጻጸሙ ለተቆጣጣሪ መ/ቤት እየታየ ለሥራ ተቋራጩ ክፍያ በሚደረግበት ጊዜ በመያዝ የሚቀር ገንዘብ ካለ መጠኑን በጽሑፍ ማረጋገጥ፣

1.2.5 የካሣ ክፍያ ጥያቆው የቀረበው ጊዜያዊ ርክክብ ከተከናወነ በኋላ ከሆነ የጊዜያዊ ርክክቡን ኮፒ መስጠት፣

1.2.6 በተለይ በአቅርቦት ውሉ መሠረት አቅራቢው ያቀረበውና ያላቀረበው ዕቃ ተለይቶ ከእነዋጋውና ለማቅረብ ያልቻለበት ምከንያት ጭምር በጹሐፍ መግለጫ መስጠት፣

1.2.7 በአቅርቦት ውሉ መሠረት ተቋራጩ¼አቅራቢው¼ የሚያቀርበው ንብረት ከውሉ ውጭ ከሆነ አሠሪው ለተቋራጩ የሰጡት የጽሑፍ ማስጠንቀቂያና አቅራቢው የሰጠው መልስ ማቅረብ፣

1.2.8 ለድርጅቱ የመዳረግ መብት (Subrogation Right) መስጠት

 · ሌሎች መረጃዎች ወይም ሰነዶች እንደ አስፈላጊነቱ ሊጠየቁ ይችላል፡