Boiler

ቦይለር ማሽን መድን Boiler and Machinery Breakdown Insurance Policy ዋስትና ለማግኘት መሟላት ያለባቸው መረጃዎች

· በድርጅቱ የተዘጋጀውን የውል መጠየቂያ ቅጽ በጥያቄው መሠረት በጥንቃቄ መሙላት· ሌሎች መረጃዎች ወይም ሠነዶች እንደ አስፈላጊነቱ ሊጠየቁ ይችላሉ፡፡
በቦይለር ማሽን መድን (Boiler and Machinery Break-down Insurance Policies) ለሚደርሱ አደጋዎች መቀረብ ያለባቸው ዋና ዋና ማስረጃዎች1.1 በቦይለር ወይም ማሽኑ ላይ ጉዳት እንደደረሰ ወዲያውኑ ለሚመለከተው ቅርንጫፉ ማሳወቅ፣

1.2 በቦይለር ወይም ማሽኑ ላይ ጉዳት ሲደርስ የደንበኛው መሐንዲስ ወይም ኃላፊ ቴክኒሽያን ስለአደጋው ዝርዝር ሁኔታ የሰጠው ሪፖርት ማቅረብ፣

1.3 የተለወጡ ዕቃዎች ዓይነት በዝርዝርና እያንዳንዳቸው የተገዙበትን ዋጋ ከደጋፊ ማስረጃዎች ጭምር ማቅረብ፣

1.4 ለሠራተኛ የተከፈለ የእጅ ዋጋ ከእነ ደጋፊ ማስረጃው ማቅረብ፣

1.5 የጥገና ሥራው በኮንትራት እንዲሠራ ካስፈለገ የኮንትራቱ ውል በሚፈጸምበት ጊዜ የድርጅቱ ሰርቬየሮች እንዲገኙ ማድረግና የጥገና ሥራው ከተከናወነ በኋላ የዕቃና የእጅ ዋጋ ተለያይቶ የዋጋ መጠየቂያ ማቅረብ፣

1.6 ጉዳት የደረሰበትን ቦይለር ወይም ማሽን ለመጠገን የሚችሉ የራሳቸው ሠራተኞች ላሏቸው ደንበኞች፣

1.6.1 የተለወጡ ዕቃዎች ዓይነት በዝርዝር እያንዳንዳቸው የተገዙበት ዋጋ ከደጋፊ ማስረጃዎች ጋር ማቅረብ፣

1.6.2 የመለዋወጫ ዕቃዎችን ደንበኛው ከውጭ አገር አዞ በቀረጥ የሚያስመጣ ከሆነ የዕቃዎች ዋጋ ለታክስና ለጉምሩክ እንዲሁም ለማጓጓዝ የተከፈለውን ስለሚያጠቃልል ደጋፊ ማስረጃዎች ማቅረብ፣

1.6.3 ለማስጠገን የወሰደውን ጊዜና ለሠራተኛ ደመወዝ የተከፈለበት የሠነድ ማስረጃ ማቀረብ፣

1.6.4 በተለይ በቦይለር መፈንዳት ምክንያት በሶስተኛ ወገን ሰውና ንብረት ላይ ጉዳት ቢያስከትል የፖሊስ ወይም ሕዝባዊ ድርጅት ሪፖርትና፣

1.6.5 እንዲሁም በቦይለር መፈንዳት ምክንያት በሶስተኛ ወገን ላይ የደረሰው ጉዳት ካሣ ጥያቄን የሚያስከትል ከሆነ ማስረጃዎች ማቅረብ፣

1.6.6 ከአደጋው የተረፉትን ንብረቶች በጥንቃቄ ማስቀመጥና እንዲጠበቁ ማድረግ፣

· ሌሎች መረጃዎች ወይም ሰነዶች እንደ አስፈላጊነቱ ሊጠየቁ ይችላል፡፡