የሕክምና ዋስትና ተጠቃሚ ግለሰቦች ሊገነዘቡዋቸው የሚቡ ዋና ዋና ነጥቦች
ታካሚው የካሣ ክፍያ ጥያቄ በሚያቀርቡበት ጊዜ የሚከተሉት ሰነዶችና ደረሰኞች መሟላት አለባቸው፣
- የህክምና ማስረጃዎች ህክምና አቅራቢው ከተመረመሩበት ቀን ጀመሮ በዘጠና ቀናት ውስጥ ለድርጅችን መቅረብ ይገባዋል፡፡
- በህክምና ካሣ ጥያቄ ማቅረቢያው ቅጽ ላይ ካሚው ወይም የሚመለተው ክፍል በመሙላች መፈረም ይኖርባቸዋል፡፡
- ታካሚው የበሽውን ዓይነትና የተመረመረበትን ቀን የማገልጽ የህክምና የምስክር ወረቀት ከከመበት ጤና ማዕከል ወይመ ተቋም ማቅረብ፣ /ሠርተፊኬት/
- በህክምና ምስክር ወረቀት መሠት የመድኃኒቶችን ማዘዣ ማያያዝ /ኘሪስክሪኘሽን/
- የምርመራው፣ የላቦራቶና ሌሎች የህክምና ወጪዎች የዋጋ ደረሰኞች የምርመራ ዓይነትና የተደረገ ወጪ በዝርዝር
- የመድኃነት ግዥ ደረሰኞች በመድኃኒት ማዘዣው መሠት የመድኃኒቱን ዓይነት፣ መጠንና ዋጋ በዝርዝር የሚገልጽ ደረሰኝ ማቅረብ፣
ማሳሰቢያ:
- . መድኃኒት መገዛት ያለበት ህጋዊ ፈቃድ ካላቸው መድኃኒት ቤቶች ሲሆን ለድንገተኛ ህክምና ካልሆነ በስተቀር በክሊኒኮች ውስጥ መድኃኒት መግዛት ክልክል ነው፡፡
- አንዳንድ የላቦራቶና ተዛማጅ ምርመራዎች ሕክምና በሚደረግበት ክሊኒክ ውስጥ የማይሰጡ ከሆኑና በሌላ ክሊኒክ ወይም የጤና ማዕከል ምርመራዎቹን ማድረግ ካሰፈለገ ምርመራዎቹ በሐኪሙ ስለመዘዛቸው የሚገልጽ ማዘዣ መያያዝ አለበት፡፡
- ተጨማሪ ማስረጃ ወየም ሰነድ እንደአስፈላጊነቱሊጠየቁ ይችላሉ፡፡