በተሽከርካሪ መድን ደንበኛው ውል ሲገቡ መጤን ያለባቸው ዋና ነጥቦች |
1. ድርጅታችን የሚሰጠው የሽከርካሪ መድን ዋስትና አይነቶችሀ. አጠቃላይ መድን ዋስትና፣ ለ. በሶስተኛ ወገን ላይ ለሚደርስ አደጋ ዋስትናና ተሽከርካሪው ላይ ለሚደርስ የእሳትና የስርቆት አደጋ ዋስትና፣ ሐ. በሶስተኛ ወገን ላይ ለሚደርስ አደጋ ዋስትና ናቸው፡፡ መ. የተሳፋሪና፣ ¼PAB & PLL¼ የሽፍታ /BSG/ ሽፋን በተጨማሪ ማግኘት ይችላሉ፡፡ 2. ስለሶስቱም የዋስትና አይነቶች አጭር መግለጫ ካገኙ በኋላ የተሽከርካሪ ባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር /ሊብሬ/ መያዝዎን ወይም ወኪል ከሆኑ የውክልና ሰነድ መያዝዎን ያረጋግጡ፡፡ 3. በውል እድሳት ወቅት ቀጣይ ዋስትና ለማግኘት ይቻል ዘንድ ማስታወሻ በአድራሻዎ አማካኝነት አስቀድሞ ይላክልዎታል፡፡ ወዲያውኑ ውሉ እንዲታደስ ፈቃደኛ መሆንዎን ፈርመው መላክ ይጠበቅብዎታል፡፡ 4. ውል በሚገቡበት ጊዜ ተሽከርካሪዎ የቅድመ አደጋ ምርመራ መደረግ ስላለበት ተሽከርካሪውን ማቅረብ ይኖርቦታል፡፡ /የድርጅት ተሽከርካሪዎችን አይመለከትም/ 5. የተሽከርካሪውን ዝርዝር መግለጫ የመድን መግበያ መጠየቂያ ቅጹ (proposal form) በሚጠይቀው መሠረት ትክክለኛውን መረጃ ያምጡ፣ አድራሻ ለውጥ እንዳደረጉ ወዲያውኑ ለድርጅቱ ያሳውቁ፡፡ 6. በተሽከርካሪዎ ላይ አደጋ ደርሶ በውሉ መሠረት የካሣ ክፍያ ሲጠየቁ በውሉ ለይ የተገለጸው የአደጋ መነሻ (Excess) ክፍያ በእርስዎ እንደሚሸፈን አይዘንጉ፡፡ 7. በውሉ ዘመን ውስጥ አደጋ ካላደረሱ በዕድሳት ወቅት የአረቦን ቅናሽ እንደ¸Ãsg”Lã ይገንዘቡ፡፡ በተጨማሪም በፈቃደኝነት የአደጋ መነሻ (voluntary excess) ከተቀበሉ የአረቦን ቅናሽ እንደ¸ÃSg”Lã ይገንዘቡ፡፡ 8. ተሽከርካሪዎ ለጥገና ሲቆም (laid up) ውሉን ማቋረጥና ተጠግኖ ሲወጣ ውሉን መቀጠል ይኖርብዎታል፡፡ የቆይታ ጊዜውን በሚመለከት የግል ተሽከርካሪ ቢያንስ ከውል ዘመን ውስጥ ለአራት ተከታታይ ሳምንታት፣ የጭነት ተሽከርካሪ ለአሥራ ሁለት ተከታታይ ሳምንታት መቆየት ይኖርበታል፡፡ 9. መድን የሚገባለት ተሽከርካሪዎ ከቀረጥ ነፃ ከሆነ ዋጋውን ለመተመን እንዲያስችል ከጉምሩክ የቀረጥ መጠኑን ማቀረብ ይጠበቅቦታል፡፡ 10. ተሽከርካሪዎን ለመንዳት የሚያስችል ሕጋዊ መንጃ ፈቃድ ሳይዙ ማሽከርከር እና ከተፈቀደው ጭነት በላይ ጭኖ ማሽከርከር እንዲሁም ዋስትና ያልተገባለት ተሳቢ ሲጎተት አደጋ ቢደርስ ሽፋን እንደሌለውና መሰናክል እንደሚሆኑ አይዘንጉ፡፡ 11. የንግድ ተሽከርካሪን በሚመለከት ለአሽከርካሪዎ ተጨማሪ የሠራተኛ ጉዳት ዋስትና መግባት እንዳለብዎ አይዘንጉ፡፡ 12. bComesa አባል አገራት ተሽከርካሪዎ በሶሶተኛ ወገን ላይ ለሚያደርሰው ጉዳት የቢጫ ካርድ በመግዛት ሽፋን የሚያገኙ መሆኑን ይገንዘቡ፣ /ወደ ጅቡቲ እና ሱዳን ክልል በተሽከርካሪው ለሚደርስ ጉዳትም ይጨምራል/ ለተሽከርካሪው አጠቃላይ ሽፋን በመግዛት የሽፋኑን መጠን ከፍ ማድረግ ይቻላል፡፡ 13. ተጨማሪ ማስረጃ ወይም ሰነድ እንደ አስፈላጊነቱ ሊጠየቁ ይችላሉ፡፡ በተሽከርካሪ ላይ አደጋ ሲደርስ ደንበኛው ማሟላት ያለባቸው ዋና ነጥቦች ካሣ 1. በንብረትዎም ሆነ በሶስተኛው ወገን አደጋ እንደደረሰ ወዲያውኑ በአቅራቢያዎ ለሚገኘው የመድን ድርጅት ቅርንጫፍ ያመልክቱ፡፡ 2. የአደጋው ሁኔታ በአፋጣኝ በትራፊክ ፖሊስ፣ በድርጅቱ ኢንስፔክተር እንዲታይ ያድርጉ፣ ተገቢውን መረጃ በመሰብሰብ እና በመስጠት የበኩልዎን ድርሻ ይወጡ፡፡ 3. ስለአደጋው አደራረስ በድርጅቱ በተዘጋጀው የአደጋ ማሳወቂያ ቅጽ ላይ የተሟላ መረጃ በመስጠት ስለተክክለኛነቱ በፊርማዎ ያረጋግጡ፡፡ ማንኛውንም የካሣ ጥያቄ በተመለከተ ከድርጅታችን እውቅና ውጪ ከሶስተኛ ወገን ጋር ድርድር ወይም ስምምነት ወይም ኃላፊነትን አይቀበሉ፡፡ 4. ተሽከርካሪዎ የጭነት ከሆነ አደጋ ከደረሰበት ቦታ ወደ ሪከቨሪ መውሰድ እነዲቻል የተጫነውን ጭነት በማራገፍ በኩል አፋጣኝ እርምጃ ይውሰዱ፡፡ 5. በንብረትዎ ላይ ጉዳት ወይም አደጋ እንደደረሰ ንብረትዎ ለበለጠ ጉዳት እንዳይጋለጥ ንብረትዎን ማስጠበቅ ይኖርብዎታል፡፡ 6. ተሽከርካሪው በባለሙያው ተመርምሮ ከጥቅም ውጭ ወይም ሙሉ ውድመት ከደረሰበት አስፈላጊውን ክፍያ ለመፈጸም ይቻል ዘንድ የሚከተሉትን ሊያሟሉ ይገባል፡፡ ሀ/ የባለቤትነት መታወቂያ ደብተር /ሊብሬ/ እና ልዩ የተሽከርካሪ ምዝገባ /ለንግድ ተሽከርካሪ/ ማቅረብ፣ ለ/ ድርጅቱ ቅሪቱን ለመሸጥ ለመለወጥ የሚያስችለው ሕጋዊ ውክልና መስጠት፣ ሐ/ ከመንገድ ትራንስፖርት አስፈላጊው የተሽከርካሪ ግብር ለመክፈልዎና እዳና እገዳ እንደሌለበት ማረጋገጫ ማቅረብ፣ መ/ ከአገር ውስጥ ገቢ መ/ቤት በተሽከርካሪው ላይ የሚፈለግ ግብር አለመኖሩን የሚገልጽ ማረጋገጫ ማቅረብ፣ ሠ/ ወኪል ከሆኑ ህጋዊ የውክልና ማስረጃ ማቅረብ፣ 7. በመጨረሻም ጥገናው ለመከናወኑ (Satisfaction Note) ፈርመው ተሽከርካሪውን መረከብ ይችላሉ፡፡ 8. በተለይ ያገለገለ ተሽከርካሪ ላይ በጥገና ወቅት በተለዋጭ እቃዎች ላይ የሚጣለውን የእርጅና መዋጮ መክፈል፣ 9. በ Comesa አባል አገራት ተሽከርካሪዎች በሶስተኛ ወገን ለሚደርሰው አደጋ ቢጫ ካርዱን ለክልሉ የኮሜሳ ቢሮ በማሳየት የካሣ መስተንግዶ ማግኘት ይችላሉ፣ 10. ሌሎች መረጃዎች እንደ አስፈላጊነቱ ሊጠየቁ ይችላሉ፡፡ |
የጨረታ፣ የመልካም ሥራ አፈጻጸም፣ የጥገና፣ የቅድሚያ ክፍያና የቀረጥ ቦንድ ለማግኘት መሟላት ያለባቸው መረጃዎች |
· የደንበኛው ስምና አድራሻ፣ · የአሠሪው ስምና አድራሻ፣ · የቦንድ አይነት፣ · ጠቅላላ የቦንድ ዋጋ፣ · አሁን የተጠየቀው የቦንድ ዋጋ፣ · የቦንድ ውል ዘመን ከ……………….. እስከ ……………….. · የተጠየቀው ቦንድ ሥራ ከአሠሪው መ/ቤት ጋር የተደረገ የውል ስምምነት ሰነድ (Contract agreement) ፎቶ ኮፒ ይቅረብ፣ · ለተጠየቀው ቦንድ የሚውል ተመጣጣኝ መያዣ (Collateral) በቅድሚያ ማስያዝና ይህንም በሕግ ፊት እንዲጸና ¥DrG½ · የተያዘው መያዣ ባለንብረቱና በመድን መ/ቤት ስም ዋስትና መግባት ያለበት መሆኑን ዋስትናውም ደንበኛው ከአሠሪው መ/ቤት ጋር ባደረገው የውል ስምምነት መሠረት የዋስትና ሽፋኑ የጊዜ ገደብ በየዓመቱ በእድሳት ተጠብቆ እንዲቆይ ¥DrG½ · የቦንዱ ሥራ ካለቀ ኦሪጅናል ቦንዱ ተመላሽ ማድረግ፡፡ ወይም አሠሪው በተሰጠው ቦንድ ላይ የካሣ ጥያቄ የሚያቀርብ መሆኑን የጽሑፍ ማረጋገጫ ¥QrB½ · ሌሎች መረጃዎች ወይም ሰነዶች እንደ አስፈላጊነቱ ሊጠየቁ ይችላል፡፡ በጨረታ፣ በመልካም ሥራ አፈጻጸም፣ በጥገና እና በአቅርቦት መድን (Bid, performance, maintenance and supply Bonds) ለሚደርሱ አደጋዎች መቅረብ ያለባቸው ዋና ዋና ማስረጃዎች 1.1.1 የጨረታ ተሳታፊዎች ስም ዝርዝርና እያንዳንዱ ተጫራች የተጫረተበትን ገንዘብ መጠን ማሳወቅ፣ 1.1.2 ለጨረታ አሸናፊው በጨረታው ውል መሠረት አሸናፊነቱ ተገልጾ የተጻፈለት ደብዳቤ ኮፒ ¥QrB¼መስጠት፣ 1.1.3 በጨረታ አሸናፊነቱ በጨረታው ውል መሠረት ፈቃደኛ ካልሆነ ፈቃደኛ ላልሆነበት ምከንያት የጽሑፍ ማስረጃ ማቅረብ፣ 1.1.4 ለድርጅቱ የመዳረግ መብት (Subrogation Right) መስጠት፣ 1.2 የመልካም ሥራ አፈጻጸምና ጥገና የአቅርቦት መድን (Performance, maintenance and supply bonds) 1.2.1 የሥራ ተቋራጩ (Contractor) በገባው ውል መሠረት ሥራውን ባለማከናወኑ ሥራውን እንዲያከናውን የተሰጠው ማስጠንቀቂያ ጽሑፍ ኮፒ ማቅረብ፣ 1.2.2 የሥራ ተቋራጩ በሥራው ውል መሠረት ገዴታውን ሊወጣ ያልቻለበት ምክንያትና ያላከናወነውን ሥራ ዝርዝር የጽሑፍ ማስረጃ ማቅረብ፣ 1.2.3 ለሥራ ተቋራጩ ለሰራው ሥራ የተከፈለውና ያልተከፈለው ቀሪ ገንዘብ ምን ያህል እንደሆነ ተለይቶና እንዲሁም ለተከፈለው ገንዘብ የሰጠው ደረሰኝ ተያይዞ የጽሑፍ ማስረጃ ማቅረብ፣ 1.2.4 በሥራ ውሉ መሠረት በየጊዜው የሥራ አፈጻጸሙ ለተቆጣጣሪ መ/ቤት እየታየ ለሥራ ተቋራጩ ክፍያ በሚደረግበት ጊዜ በመያዝ የሚቀር ገንዘብ ካለ መጠኑን በጽሑፍ ማረጋገጥ፣ 1.2.5 የካሣ ክፍያ ጥያቆው የቀረበው ጊዜያዊ ርክክብ ከተከናወነ በኋላ ከሆነ የጊዜያዊ ርክክቡን ኮፒ መስጠት፣ 1.2.6 በተለይ በአቅርቦት ውሉ መሠረት አቅራቢው ያቀረበውና ያላቀረበው ዕቃ ተለይቶ ከእነዋጋውና ለማቅረብ ያልቻለበት ምከንያት ጭምር በጹሐፍ መግለጫ መስጠት፣ 1.2.7 በአቅርቦት ውሉ መሠረት ተቋራጩ¼አቅራቢው¼ የሚያቀርበው ንብረት ከውሉ ውጭ ከሆነ አሠሪው ለተቋራጩ የሰጡት የጽሑፍ ማስጠንቀቂያና አቅራቢው የሰጠው መልስ ማቅረብ፣ 1.2.8 ለድርጅቱ የመዳረግ መብት (Subrogation Right) መስጠት · ሌሎች መረጃዎች ወይም ሰነዶች እንደ አስፈላጊነቱ ሊጠየቁ ይችላል፡፡ |
ቦይለር ማሽን መድን Boiler and Machinery Breakdown Insurance Policy ዋስትና ለማግኘት መሟላት ያለባቸው መረጃዎች |
· በድርጅቱ የተዘጋጀውን የውል መጠየቂያ ቅጽ በጥያቄው መሠረት በጥንቃቄ መሙላት· ሌሎች መረጃዎች ወይም ሠነዶች እንደ አስፈላጊነቱ ሊጠየቁ ይችላሉ፡፡ 1.2 በቦይለር ወይም ማሽኑ ላይ ጉዳት ሲደርስ የደንበኛው መሐንዲስ ወይም ኃላፊ ቴክኒሽያን ስለአደጋው ዝርዝር ሁኔታ የሰጠው ሪፖርት ማቅረብ፣ 1.3 የተለወጡ ዕቃዎች ዓይነት በዝርዝርና እያንዳንዳቸው የተገዙበትን ዋጋ ከደጋፊ ማስረጃዎች ጭምር ማቅረብ፣ 1.4 ለሠራተኛ የተከፈለ የእጅ ዋጋ ከእነ ደጋፊ ማስረጃው ማቅረብ፣ 1.5 የጥገና ሥራው በኮንትራት እንዲሠራ ካስፈለገ የኮንትራቱ ውል በሚፈጸምበት ጊዜ የድርጅቱ ሰርቬየሮች እንዲገኙ ማድረግና የጥገና ሥራው ከተከናወነ በኋላ የዕቃና የእጅ ዋጋ ተለያይቶ የዋጋ መጠየቂያ ማቅረብ፣ 1.6 ጉዳት የደረሰበትን ቦይለር ወይም ማሽን ለመጠገን የሚችሉ የራሳቸው ሠራተኞች ላሏቸው ደንበኞች፣ 1.6.1 የተለወጡ ዕቃዎች ዓይነት በዝርዝር እያንዳንዳቸው የተገዙበት ዋጋ ከደጋፊ ማስረጃዎች ጋር ማቅረብ፣ 1.6.2 የመለዋወጫ ዕቃዎችን ደንበኛው ከውጭ አገር አዞ በቀረጥ የሚያስመጣ ከሆነ የዕቃዎች ዋጋ ለታክስና ለጉምሩክ እንዲሁም ለማጓጓዝ የተከፈለውን ስለሚያጠቃልል ደጋፊ ማስረጃዎች ማቅረብ፣ 1.6.3 ለማስጠገን የወሰደውን ጊዜና ለሠራተኛ ደመወዝ የተከፈለበት የሠነድ ማስረጃ ማቀረብ፣ 1.6.4 በተለይ በቦይለር መፈንዳት ምክንያት በሶስተኛ ወገን ሰውና ንብረት ላይ ጉዳት ቢያስከትል የፖሊስ ወይም ሕዝባዊ ድርጅት ሪፖርትና፣ 1.6.5 እንዲሁም በቦይለር መፈንዳት ምክንያት በሶስተኛ ወገን ላይ የደረሰው ጉዳት ካሣ ጥያቄን የሚያስከትል ከሆነ ማስረጃዎች ማቅረብ፣ 1.6.6 ከአደጋው የተረፉትን ንብረቶች በጥንቃቄ ማስቀመጥና እንዲጠበቁ ማድረግ፣ · ሌሎች መረጃዎች ወይም ሰነዶች እንደ አስፈላጊነቱ ሊጠየቁ ይችላል፡፡ |
የአደጋ እና የአሠሪ ግዴታ መድን Personal Accident and Workmen’s Compensation Policy ዋስትና ለማግኘት መሟላት ያለባቸው መረጃዎች፣
ሀ. የሠራተኞች /ዋስትና የተገባላቸው ሰዎች ስም ዝርዝር ማቅረብ፣
ለ. የሠራተኞች /ዋስትና የተገባላቸው ሰዎች ዕድሜ /በስም የተጠቀሱ ከሆነ/ ዝቅተኛው 14 ዓመት ከፍተኛው 65 ዓመት መብለጥ የለበትም፣
ሐ. ዋስትና የተገባው ስም ሳይጠቀስ ከሆነ /በመ/ቤቱ/ፋብሪካ ወዘተ./ ያሉቱን ሁሉንም ሠራተኞች ማጠቃለል ይኖርበታል፣
መ. የሠራተኞች /ዋስትና/ የተገባላቸው ሰዎች የሥራ ጸባይ /ባሕሪ/፣
ሠ. የሠራተኞች /ዋስትና/ የተገባላቸውን ሰዎች ደሞዝ ማሳወቅ፣
ረ. በውል ዘመኑ የተከፈለውን የደመወዝ መጠን በዓመቱ መጨረሻ ማሳወቅ እንዳለብዎ አየዘንጉ፣
• ሌሎች መረጃዎች ወይም ሰነዶች እንደ አስፈላጊነቱ ሊጠየቁ ይችላል፡፡ በአደጋና የአሠሪ ግዴታ መድን (Personal Accident and Workmen’s Compensation Policy) ለሚደርሱ አደጋዎች መቅረብ ያለባቸው ዋና ዋና ማስረጃዎች
1.1 የሞት አደጋን በሚመለከት
1.1.1 ስለሞት አደጋው ለሚመለከተው ቅርንጫፍ ማሳወቅ፣
1.1.2 የፖሊስ ሪፖርት ማቅረብ፣
1.1.3 የአሟሟቱን ሁኔታ የሚገልጽ የሬሣ ምርመራ የሐኪም ማስረጃ ማቅረብ፣
1.1.4 የሕጋዊ ወራሾች የፍርድ ቤት ውሳኔ ማቅረብ፣
1.1.5 በተለይ በአሠሪ ግዴታ መድን አደጋው በደረሰ ጊዜ ለሠራተኛው ይከፈለው የነበረው የወር ደመወዝ ማስረጃ፣
1.1.6 አሟሟቱ ከሥራ ባህሪ በመነጨ ከሆነ ከመ/ቤቱ በቂ ማብራሪያ በወቅቱ ማቅረብ፣
1.2 በአካል ላይ ለሚደርሱ ጉዳቶች
1.2.1 ስለደረሰው አደጋ ለሚመለከተው ቅርንጫፍ ማሳወቅ፣
1.2.2 ለቋሚ የአካል ጉድለት የህክምና ቦርድ ማስረጃ ማቅረብ፣
1.2.3 ለሕመም ፈቃድ የሐኪም ማስረጃ ማቅረብ፣
1.2.4 መድኃኒት እንዲገዛ ሐኪም ያዘዘበት ማስረጃ ማቅረብ፣
1.2.5 መድኃኒት የገዛበትና የህክምና ወጪ ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ፣
1.2.6 ሠራተኞች ከቤት ወደ ቢሮ ወይም ከቢሮ ወደ ቤት ሲጓዙ ጉዳት ከደረሰባቸው አደጋ የደረሰበትን ሰዓትና ቦታ ለፖሊስ/ሕዝባዊ ድርጅት ማስመዝገብ፡፡
1.2.7 ለሠራተኛው ይከፈለው የነበረ ወቅታዊ ደሞዙን መግለጽ፣
የአደጋእና የአሠሪ ግዴታ መድን Personal Accident and Workmen’s Compensation Policy ዋስትና ለማግኘት መሟላት ያለባቸው መረጃዎች፣
1.1 የሞት አደጋን በሚመለከት
1.1.1 ስለሞት አደጋው ለሚመለከተው ቅርንጫፍ ማሳወቅ፣
1.1.2 የፖሊስ ሪፖርት ማቅረብ፣
1.1.3 የአሟሟቱን ሁኔታ የሚገልጽ የሬሣ ምርመራ የሐኪም ማስረጃ ማቅረብ፣
1.1.4 የሕጋዊ ወራሾች የፍርድ ቤት ውሳኔ ማቅረብ፣
1.1.5 በተለይ በአሠሪ ግዴታ መድን አደጋው በደረሰ ጊዜ ለሠራተኛው ይከፈለው የነበረው የወር ደመወዝ ማስረጃ፣
1.1.6 አሟሟቱ ከሥራ ባህሪ በመነጨ ከሆነ ከመ/ቤቱ በቂ ማብራሪያ በወቅቱ ማቅረብ፣
1.2 በአካል ላይ ለሚደርሱ ጉዳቶች
1.2.1 ስለደረሰው አደጋ ለሚመለከተው ቅርንጫፍ ማሳወቅ፣
1.2.2 ለቋሚ የአካል ጉድለት የህክምና ቦርድ ማስረጃ ማቅረብ፣
1.2.3 ለሕመም ፈቃድ የሐኪም ማስረጃ ማቅረብ፣
1.2.4 መድኃኒት እንዲገዛ ሐኪም ያዘዘበት ማስረጃ ማቅረብ፣
1.2.5 መድኃኒት የገዛበትና የህክምና ወጪ ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ፣
1.2.6 ሠራተኞች ከቤት ወደ ቢሮ ወይም ከቢሮ ወደ ቤት ሲጓዙ ጉዳት ከደረሰባቸው አደጋ የደረሰበትን ሰዓትና ቦታ ለፖሊስ/ሕዝባዊ ድርጅት ማስመዝገብ፡፡
1.2.7 ለሠራተኛው ይከፈለው የነበረ ወቅታዊ ደሞዙን መግለጽ፣
የገንዘብ Money Insurance Policy ዋስትና ለማግኘት መሟላት ያለባቸው መረጃዎች |
· በድርጅቱ የተዘጋጀውን የውል መጠየቂያ ቅጽ በጥያቆው መሠረት በጥንቃቄ መሙላት፣ · ገንዘብ ወደ ባንክ ወይንም ከባንክ በሚያወጡበት ወቅት ገንዘቡ ከብር 10,000 /አሥር ሺህ/ በላይ ከሆነ ተሽከርካሪና የጥበቃ ኃይል እንዲኖርዎት ያድርጉ፣ · ለሎች መረጃዎች ወይም ሠነዶች እንደ አስፈላጊነቱ ሊጠየቁ ይችላሉ፣ 1 የፖሊስ ወይም የፖሊስ ጣቢያ በሌለበት የሕዝባዊ ድርጅት ሪፖርት፣ · ሌሎች መረጃዎች ወይም ሰነዶች እንደ አስፈላጊነቱ ሊጠየቁ ይችላል፡፡ |
ለማሪን የውል ጥያቄ የሚከተለትን መሠረታዊ ሠነዶች ማቅረብ አስፈላጊ ይሆናል፡ |
1.በድርጅታችን የተዘጋጀውን የማመልከቻ ቅጽ /ቢጫ/ -ድጵቸለቷረቷተፀጸነ ስለፀፐ? መሙላት ወይም2. የሚጓጓዘውን ንብረት በተመለከተ አስፈላጊውን መረጃ ሁሉ በማካተት ጠያቂው ድርጅት በጽሑፍ ሊያቀርብ ይችላል፡፡ ደብዳቤው የሚከተሉትን መረጃዎች ማካተት ይኖርበታል፡፡ · የድርጅቱ /የመድን ገቢው/ ሙሉ አድራሻ ፖ.ሣ.ቁጥር ………………………… · የዕቃው ዓይነት፣ ብዛት፣ ዋጋ 3. ኘሮፎርማ -ፕረጸፈጸረመቷ ፅነቨጸፀቸጵ?እና እንደ አስፈላጊነተ ፕጭረቸሀቷሰጵ ቕረደጵረ ንጸ.እናሌሎች ደጋፊ ሠነዶችን ማቅረብ፣ 4. እንደ አስፈላጊነቱ ሽፋኑን ማራዘም አተጵነሰፀጸነ ፕጵረፀጸደ? ካስፈለገ በአየር ለሚጓጓዙ የ3ዐ ቀን፣ በመርከብ /ባሕር/ ለሚጓጓዙ የ6ዐ ቀን ጭማሪ በጽሑፍ ማቅረብ ይቻላል፡፡ በባህርና በአየር ለሚጓጓዙ ዕቃዎች በተጓጓዘው ንብረት ላይ ብልሽት ወይም ጉድለት በሚከሰትበት ወቅት ደንበኛው በጽሑፍ ከሚያቀርበው የካሣ ክፍያ ጥያቄ ጋር የሚከተሉት ሠነዶች መቀረብ ይኖርባቸዋል ሀ/ በባሕር ወይም በየብስ ለሚመጣ ዕቃ፣ 1. ኦሪጅናል የኢንሹራንስ ውል (Certificate/Policy) 2. ኦሪጅናል የላኪው ድርጅት drs” (Commercial Invoice) 3. ኦሪጅናል የመርከብ ማጓጓዣ ሠነድ (Bill of Lading) 4. መርከቡ የገባበትን ቀን የሚገልጽ ሠነድ (vessel arrival notification slip) 5. የመንገድ ወረቀት (Truck Way Bill, store issue voucher, dispatch note) 6. የሰርቬይ ሪፖርት (Preliminary Survey Report) 7. አንድ እሽግ ወይም ከዚያ በላይ መርከቧ እግረመንገዷን ባረፈችበት ወደብ በስህተት በመራገፉና በመጥፋቱ ምክንያት የቀረበ የካሣ ጥያቄ ከሆነ ጉድለቱን የሚያሳይ ሠነድ “Shortianded Certificate” 8. በንብረቱ ላይ ብልሽት ወይም ጉድለት በሚታይበት ወቅት ወዲያውኑ ለአጓጓዡ ወይም ለወኪሉ የይከፈለኛል ጥያቄ ማቅረብ የባለንብረቱ መብት በመሆኑ 9. እንደአስፈላጊነቱ የጉምሩክ ዲክላራሲዮን 10. የካሣ መጠን ስሌት (Loss Assessment) ማያያዝ 11. ሌሎች ማስረጃ ወይም ሰነድ እንደ አስፈላጊነቱ ይጠየቃል 12. በጉዞ ላይ ለጠፋው ንብረት ለድርጅታችን የመዳረግ መብት ለ/ በአውሮኘላን ለሚመጣ ዕቃ፣ 1. ኦሪጅናል የኢንሹራንስ ውል (Certificate/Policy) 2. ኦሪጅናል የላኪው ድርጅት drsSÂ (Commercial Invoice) እንደ አስፈላጊነቱ 3. የአውሮኘላን ማጓጓዣ ሠነድ (Airway Bill) 4. አውሮኘላኑ የገባበትን ቀን የሚያሳይ ሰነድ (Delivery Order of Customs 5. አንድ እሽግ ወይም ከዚያ በላይ አውሮኘላኑ እግረመንገዱን በአረፈበት 6. በንብረቱ ላይ ጉድለት ወይም ብልሽት በሚታይበት ወቅት ወዲያውኑ 7. የካሣ መጠን ስሌት (Loss Assessment) ማያያዝ 8. ሌሎች ማስረጃ ወይም ሰነድ እንደ አስፈላጊነቱ ይጠየቃል 9. በጉዞ ላይ ለጠፋው ንብረት ለድርጅታችን የመዳረግ መብት ማሳበቢያ አንድ ንብረት በየትኛውም ዓይነት ማጓጓዣ ሊመጣ ይችላል፡፡ ሆኖም እሽጉ በምንም መልኩ በርክክብ ወቅት ብልሽት ወይም ጉድለት በሚታይበት |
Fire & Burglary
የእሣትና ቃጠሎ በተመለከተ ለሚደረርሱ አደጋዎች መቅረብ ያለባቸው መረጃዎች
|
የሶስተኛ ወገን የኃላፊነት ሕጋዊ ግዴታ መድን Public Liability Policy ዋስትና ለማግኘት መሟላት ያለባቸው መረጃዎች፣ |
· በድርጅቱ የተዘጋጀውን የውል መጠየቂያ ቅጽ በጥያቄው መሠረት በጥንቃቄ መሙላት፣· ሌሎች መረጃዎች ወይም ሠነዶች እንደ አስፈላጊነቱ ሊጠየቁ ይችላሉ፡፡ 1.1 በሰው ላይ ለሚደርስ የሞት አደጋን በሚመለከት፣ 1.1.1 የፖሊስ ሪፖርት ማቅረብ፣ 1.1.2 አደጋው እንደደረሰ ስለአደጋው ለሚመለከተው ቅርንጫፍ ማሳወቅ፣ 1.1.3 የአሟሟቱን ሁኔታ የሚገልጽ የሬሣ ምርመራ የሐኪም ማስረጃ ማቅረብ፣ 1.1.4 የሕጋዊ ወራሾች የፍርድ ቤት ውሳኔ ማቅረብ፣ 1.2 በሰው ላይ ለሚደርስ የአካል ጉድለት 1.2.1 ለቋሚ የአካል ጉድለት የህክምና ቦርድ ማስረጃ ማቅረብ፣ 1.2.2 ለሕመም ፈቃድ የሀኪም ማስረጃ ማቅረብ፣ 1.2.3 መድኃኒት እንዲገዛ ሐኪም ያዘዘበት ማስረጃ ማቅረብ፣ 1.2.4 መድኃኒት የተገዛበትና የህክምና ወጪ ሕጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ፣ 1.2.5 የሕክምና ማስረጃ ሠርተፊኬት ማቅረብ፣ 1.3 በንብረት ላይ ለሚደርስ ጉዳት /የደረሰበት ንብረት ዝርዝርና ግምታዊ ዋጋ/፣ 1.3.1 ከፖሊስ/ሕዝባዊ ድርጅት ሪፖርት ማቅረብ፣ 1.3.2 ስለጉዳት መጠኑ የባለሙያ ግምት ማቅረብ፣ 1.4 በጠፋው ንብረት ለድርጅቱ የመዳረግ መብት (Subrogation Right) መስጠት፣ 1.5 ከጉዳት የተረፈውን ንብረት በጥንቃቄ ማስቀመጥና እንዲጠበቅ ማድረግ፣ · ሌሎች መረጃዎች ወይም ሰነዶች እንደ አስፈላጊነቱ ሊጠየቁ ይችላል፡፡ |
በዕምነት ማጉደል መድን Fidelity Guarantee Policy ዋስትና ለማግኘት መሟላት ያለባቸው መረጃዎች
በዕምነት ማጉደል መድን (Fidelity Guarantee Policy) ለሚደርሱ አደጋዎች መቅረብ ያለባቸው ዋና ዋና ማስረጃዎች
1 . የዕምነት መጉደሉ እንደደረሰ ወዲያውኑ ለሚመለከተው ቅርንጫፍ ማሳወቅ
2 . ዕምነት ያጐደለው ሠራተኛ መተማመኛ ካልፈረመ የፖሊስ ሪፖርት፣
3 . የኦዲተር ሪፖርት ማቅረብ፣
4 . ዕምነት ያጐደለው ሠራተኛ መተማመኛ ካልሰጠ የፍርድ ቤት ውሳኔ፣
5 . ለዕምነት አጉዳዩ የሚከፈል ገንዘብ ካለ ምሳሌ ደመወዝ አበል ወዘተ የተያዘ መሆኑን ማረጋገጫ ጽሁፍ፣
6 . የዕምነት አጉዳዩ ትክክለኛ አድራሻ፣ ከተማ፣ ከፍተኛ፣ ቀበሌ፣ የቤት ቁጥር
7 . የዕምነት አጉዳዩ ተንቀሳቃሽ ወይም የማይንቀሳቀስ ንብረት ካለው እንዲገለጽ ማድረግ፣
8 . ለጠፋው ገንዘብ ለድርጅቱ የመዳረግ መብት (Subrogation Right) መስጠት፣
· ሌሎች መረጃዎች ወይም ሰነዶች እንደ አስፈላጊነቱ ሊጠየቁ ይችላል፡፡